ግእዝን ለምን እናጠናለን?
ኢትዮጵያውያን በመሆናችን
ግእዝ ቋንቋ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቋንቋ በመሆኑ የግእዝን ቋንቋ ማወቃችን በብዙ ጥበብ የተሞሉ መጻሕፍትን ለማወቅና ለመመርመር ትልቅ ጥቅም ያለው በመሆኑ
ስለ ኢትዮጵያ ምንነት ማወቅ ከፈለግን ግእዝ ቋንቋ መማር እጅግ አስፈላጊ ነው። የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያሳዩ ብዙ መጻሕፍት የተጻፉት በግእዝ ቋንቋ ነው። ብዙ ሊቃውንት የግእዝ ቋንቋን ዘመን የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ነበር ይላሉ።
ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ግእዝ ቋንቋ የሐገራችን ጥንታዊ ቋንቋ ከመሆኑ በተጨማሪ ስለመንፈሳዊ ነገሮች ለማወቅ መሠረታዊ እና ቁልፍ ነገር ነው።
የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በብዛት የተጻፉት በግእዝ ቋንቋ ነው አብዛኛዎቹ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ወደ አማርኛ አልተተረጎሙም።
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶችም በሙሉ የተደረሱት በግእዝ ቋንቋ ነው
ዜማ ለመማር የሚፈልግ ሰው መጀመሪያ ግእዝን ቢማር የመጻሕፍቱን ምሥጢር እንዲረዳ ስለሚያግዘው ከዜማው በፊት ቋንቋውን አስቀድሞ እንዲማር ይመከራል። ዜማ ሲዜም የግእዝ ንባባት ስርዓትን ጠብቆ ነው።
የግእዝ ቋንቋን ጥቅም ያወቁ
ብዙ የውጪ አገር ዜጎች እንኳን የኢትዮጵያን ጥበብና እውቀት ለመረዳት ግእዝ ቋንቋን ያጠናሉ
ሃያ ስምንት የሚሆኑ አገራት ግእዝ ቋንቋን በየዩኒቨርስቲያቸው
ይሰጣሉ።